Wednesday, April 16, 2025

የዐቃቤ ሕግ ምንነት

ዐቃቤ ህግ

“ዐቃቤ ሕግ” የሚለው መጠሪያ የያዘው ሁለት ቃላትን ነው፡፡ “ዐቃቤ” የሚለው ቃል “ዐቀበ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የመነጨ ሲሆን ትርጉሙም ጠበቀ ማለት ነው፡፡ ይህ የሚያስገነዝበው “ዐቃቤ ሕግ” ማለት “የሕግ ጠባቂ” ማለት መሆኑን ነው፡፡

ዐቃቤ ሕግ ስሙ እንደሚያመለክተው የሕግ ጠባቂ ወይም ሕግ አስከባሪ ማለት ነው፡፡ ማንኛውም  የመንግሥት አካል በተለይ ሕግ አስፈጻሚው በተቋቋመበት አዋጅ በተለየ በተሰጠው ሥልጣንና ተግባር መሠረት የተቋቀመበትን ሕግ የማስፈጸም ግዴታ አለበት፡፡ ነገር ግን ዐቃቤ ሕግን ስንመለከት ከእነዚህ መንግሥታዊ አካላት የተለዬ ነው፡፡ ዐቃቤ ሕግ የሚያስከብረው የተቋቋመበትን አዋጅ ብቻ አይደለም፤ ሕግ  አውጪው ያወጣቸው ሕጐች በሙሉ መከበራቸውን የመከታተል ኃላፊነት አለበት፡፡

የዐቃቤ ሕግ ትርጉም ይህን ሲመስል በአገራችን በተለይ ዐቃቤ ሕግ የሚለው መጠሪያ የሚታወቀው ግን  እላይ ካስቀመጥነው ትክክለኛ ትርጉም አንፃር ሳይሆን ወንጀል ለመፈጸሙ በቂ ማስረጃ ሲቀርብለት  ወንጀሉን ፈጸመ በተባለው ሰው ላይ መንግስትን ወክሎ ክስ የማቅረብና መከራከር ተግባር ብቻ የያዘ ተቋም ተደርጐ ሲወሰድ ነው የሚታየው ፡፡


ዐቃቤ ሕግ ሕግ አውጭው ያወጣው የወንጀል ሕግ በተጣሰ ጊዜ ሕጉን ወክሎ በችሎት የወንጀል ክስ የማቅረብና የማስቀጣት ኃላፊነት ያለበት ቢሆንም ይህ ከተሰጡትተግባራት መካከል አንዱ የስራ ድርሻው  ሲሆን ዐቃቤ ሕግ በዚህ ብቻ ሳይወሰን ከላይ እንደጠቆምነው ሕግ አውጭው ያወጣቸውን ማናቸውንም ሕጐች የማስከበር ሥልጣንና ኃላፊነት የተቀበለ አካል ነው፡፡ ስለሆነም በወንጀል ጉዳይ ምርመራ እንዲካሄድ ማድረግ (ወይም ምርመራውን ራሱ ማካሄድ)፣ የወንጀል ክስ አቅርቦ መከራከር ወ.ዘ.ተ. ለዐቃቤ ሕግ  ከተሰጡት ተግባራት ውስጥ ከፊሉ ተብሎ ሊወሰድ የሚችል እንጅ የዐቃቤ ሕግ ሥራ በወንጀል ዙሪያ ብቻ የተገደበ አይደለም፡፡


ከፍትህ ሚኒስትር ፌስቡክ ገፅ የተገኘ

No comments:

Post a Comment

የዐቃቤ ሕግ ምንነት

ዐቃቤ ህግ “ዐቃቤ ሕግ” የሚለው መጠሪያ የያዘው ሁለት ቃላትን ነው፡፡ “ዐቃቤ” የሚለው ቃል “ዐቀበ” ከሚለው የግዕዝ ቃል የመነጨ ሲሆን ትርጉሙም ጠበቀ ማለት ነው፡፡ ይህ የሚያስገነዝበው “ዐቃቤ ሕግ” ማለት “የሕግ ጠባቂ...